የዓም ሃይማኖቶች የመቻቻል መንፈስ መዳበር ለህዝቦች የጋራ መስተጋብር እንቅስቃሴዎች ሁኔታዎችን የሚያመቻች መሆኑን የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ገለፁ፡፡
የመጀመሪያው የዓለም ሃይማኖቶችና እምነቶች የመቻቻል ሳምንት ከስልሳ ሀገራት የተውጣጡና የተያዩ ሃይማኖቶችና እምነቶችን የወከሉ በርካታ ተሳታዊዎች በተገኙበት በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በዛሬው እለት ተከበሯል፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ በእለቱ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር የሃይማኖት መቻቻልና መከባበር ሳምንት መከበሩ በህዝቦች መካከል ያሉ ሌሎች የጋራ መስተጋብሮችን በሰላም ለማከናወን ቁልፍ ሚና ይኖረዋል፡፡
ኢትዮጵያ በርካታ ሃይማኖቶችና እምነቶች በመቻል ለበርካታ ዘመናት የኖሩባት ሀገር በመሆኗ የመጀመሪያው የዓለም ሃይማኖቶች የመቻቻል ሳምንት በኢትዮጵያ መከበሩ ተገቢ መሆኑን ክቡር ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment