Wednesday, March 21, 2018

“የናይል ተፋሰስ የውሃ ሀብትን ለዘላቂ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል ያስፈልጋል” ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

የቀጠናው ሀገራት የጋራ ተግዳሮቶች መበራከት ለናይል ተፋሰስ ሀገራት ኢኒሸቲቭ መመስረት መነሻ ምክንያት እንደሆነ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡረ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ገለፁ፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ 12ኛውየናይል ተፋሰስ ኢኒሸቲቭ ቀን በዓልን የተመለከተ ዝግጅት በተባበሩት መንግስታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ዛሬ ረፋድ ላይ ከፍተዋል፡፡

 https://youtu.be/R45jIbV-HRk


በመክፈቻው ስነስርዓት ላይ ክቡር ፕሬዝደንቱ ባደረጉት ንግግር የናይል ተፋሰስ ኢንሸቲቭ መመስረት መሰረታዊ መነሻው በተፋሰሱ ያሉ ሀገራት የጋራ ችግራቸውን በጋራ ጥረት ለማስወገድ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የቀጠናው ህዝቦች በከፍተኛ ድህነት ውስጥ መኖራቸው፣ ኋላቀር የግብርና ዘዴ የሚጠቀሙ መሆናቸው፣ ያልተመጣጠነ የህዝብ ቁጥር መጨመር እና ለአየር ፀባይ ለውጥ ተጋላጭነት የቀጠናው ከባድ ተግዳሮቶች መሆናቸውን ክቡር ፕሬዝደንቱ አብራርተዋል፡፡

ከእነዚህ ተግዳሮቶች የተነሳ የቀጠናው ህዝብ ለምግብ፣ ለትምህርት፣ ለጤና፣ ለንፁህ መጠጥ ውሃ እና ለሃይል ስርጭት እጥረት የተጋለጡ መሆናቸውን ጨምረው ጠቅሰዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ሙሉ ለሙሉ በመፍታት በቀጠናው የተሻለ ሰላም፣ የፖለቲካ መረጋጋትና ሀገራቱን ያማከለ ኢኮኖሚያዊ ውህደት እንዲኖር ህዝብንና የግሉን ሴክተር አቀናጅቶ በትብብር መስራት እንደሚያስፈልግ ክቡር ፕሬዝደንቱ ጠቁመዋል፡፡

የናይል ተፋሰስ ኢኒሸቲቭ እኤአ ፌብሩዋሪ 22 ቀን 1999 የተመሰረተ ሲሆን ቀኑ መከበር ከተጀመረ 12 ጊዜው ነው፡፡ የዚህን ቀን መታሰቢያ በዓል እኤአ በ2008፣ በ2013 እና በ2018 በአባል ሀገራቱ በጋራ ኢትዮጵያ ውስጥ እንደተከበረ ለማወቅ ተችሏል፡፡ 

የናይል ተፋሰስ ኢኒሸቲቭ ሀገራት አስር ሲሆኑ እነሱም ቡሩንዲ፣ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ ግብፅ፣ ኢትዮጵያ፣ ኬኒያ፣ ሩዋንዳ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ሱዳን፣ ታንዛኒያ እና ዩጋንዳ ናቸው፡፡ 



“Nile Basin Water Must be Used for Sustainable Economic Integration” H.E. President Dr. Mulatu Teshome

“The basic reason for the establishment of the Nile Basin Initiative (NBI) is the common challenge that faced member countries,” said H.E. Dr. Mulatu Teshome, President of the Federal Democratic Republic of Ethiopia.

H.E. the President opened the 12th NBI day celebration event program at ECA hall today 22nd February 2018.

In his speech during the opening, H.E. the President said that sustainable socioeconomic development comes through the equitable utilization of the common Nile basin water resources.

He added that the people in the region (NBI) face challenges like extreme poverty, limited productivity agricultural activities, highly pressured urbanization and climate change effects.

Due to these, the people in the region are vulnerable for shortage of food, sanitation, education, pure water supply, health centers, energy, etc. … the President elaborated further. 

Hence, it is mandatory to restore peace, political stability, economic integration and prosperity through unity, cooperation and coordination being in harmony, the President added.

NBI was found 22nd February 1999 and the commemorating of this day is just for its 12. Ethiopia hosted this day for the third time; the previous were in 2008 and 2013.

Member countries of NBI are ten: namely, Burundi, DR Congo, Egypt, Ethiopia, Kenya, Rwanda, South Sudan, The Sudan, Tanzania and Uganda. Eritrea participates as an observer.

No comments:

Post a Comment