Showing posts with label videos. Show all posts
Showing posts with label videos. Show all posts

Wednesday, March 21, 2018

“ሀገር ሆኖ ጎረቤት መምረጥ አይቻልም” ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በጋምቤላ ክልል የሶስት ቀናት ጉብኝት በማድረግ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማየት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተወያይተዋል፡፡

“የናይል ተፋሰስ የውሃ ሀብትን ለዘላቂ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማዋል ያስፈልጋል” ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ

የቀጠናው ሀገራት የጋራ ተግዳሮቶች መበራከት ለናይል ተፋሰስ ሀገራት ኢኒሸቲቭ መመስረት መነሻ ምክንያት እንደሆነ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡረ ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ገለፁ፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ 12ኛውየናይል ተፋሰስ ኢኒሸቲቭ ቀን በዓልን የተመለከተ ዝግጅት በተባበሩት መንግስታት ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ ዛሬ ረፋድ ላይ ከፍተዋል፡፡

 https://youtu.be/R45jIbV-HRk

የኢፌዴሪ ኘሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የተለያዩ ሀገራትን አምባሳደሮች የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

ተቀማጭነታቸው በአዲስ አበባ የሆኑና ዛሬ ጠዋት በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተዘጋጀው ስነ ስርአት ላይ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለክቡር የኢፌዴሪ ኘሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ያቀረቡት የኒውዚላንድ አምባሳደር ማርክ ራፋኤል ራምስደነ፣  የኮሪያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ሊም ሁን-ሚን፣ የፖርቹጋል አምባሳደር ሚስስ ሄሌና ማሪያ ሮድሪገስ ፈርናንዴዝ ማልካታ፣ የጆርጂያ ሪፐብሊክ አምባሳደር ዙራብ ድቫሊሽቪሊ፣ የቦስኒያ ሄርዞጎቪና አምባሳደር ደስኮ ስቶጃንቪች እና የኔፓል አምባሳደር ጂሀቢንድራ ፒ.አርያል ናቸው። 

ክቡር ፕሬዝደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የዓለም ዋንጫን ተቀበሉ

የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ ወደ ኢትዮጵያ መምጣቱ በእግር ኳስ ክህሎታቸው ወደፊት ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረስ ለሚፈልጉ ታዳጊ ወጣቶች ከፍተኛ መነሳሳትን እንደሚፈጥር የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ተናገሩ፡፡