የኢትዮጵያ
ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ክቡር ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ በጋምቤላ ክልል የሶስት ቀናት ጉብኝት
በማድረግ የተለያዩ የልማት እንቅስቃሴዎችን በማየት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር ተወያይተዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ ከህዝብ ጋር በነበራቸው ውይይት ህብረተሰቡ ከደቡብ ሱዳን የሚነሳው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት ያስቸገራቸው መሆኑን የ2008ቱን ጭፍጨፋ በአብነት በጥቀስ አስፈላጊው መከላከል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ ከህዝብ ጋር በነበራቸው ውይይት ህብረተሰቡ ከደቡብ ሱዳን የሚነሳው የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት ያስቸገራቸው መሆኑን የ2008ቱን ጭፍጨፋ በአብነት በጥቀስ አስፈላጊው መከላከል እንዲደረግላቸው ጠይቀዋል፡፡
ሀገር ሆኖ ጎረቤት መምረጥ ስለማይቻል የደቡብ ሱዳን ጎረቤት ሀገር እስከሆን ድረስ ካላት የፖለቲካ አለመረጋጋት የተነሳ ተወያይቶ ተጨባጭ መፍትሔ ላይ መድረስ አዳጋች መሆኑን ክቡር ፕሬዝደንቱ ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ስጋቱን በከፍተኛ ሁኔታ ለመቀነስ ብሎም ለማስቀረት አስፈላጊው ሁሉ ትግል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
ክቡር
ፕሬዝደንቱ በጋምቤላ ቆይታቸው የቸቦኬር መንደር ምስረታ፣ የአሌሮ የመስኖ ግድብ፣ የሳውዲ ስታር ግብርና ልማት እና
የካራቱሬ የተቀናጀ እርሻ ፕሮጀትን ጎብኝተዋል፡፡ ከዚህም ሌላ በተለያዩ መድረኮች ከህዝብና ከክልሉ አመራሮች ጋር
ተወያይተዋል፤ በሙርሌ ጎሳ ታጣዊዎች ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች መታሰቢያ በተዘጋጀ መርሀ-ግብር ላይ ታድመው ንግግር
አድርገዋል፡፡
ክቡር ፕሬዝደንቱ በንግግራቸውም የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ዘግናኝ ድርጊት መላው የኢትዮጵያ ህዝብንና የኢፌዴሪ መንግስትን እጅግ የስቆጣና ያሳዘነ ድርጊት እንደነበር ጠቅሰው መንግስት የሦስት ቀናት በሔራዊ ሀዘን በማወጅ እና የሀገሪቱ ሰንደቅ አላማ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ከጋምቤላ ህዝብ ጎን መቆሙን እንዳረጋገጠ ተናግረዋል፡፡
አያይዘውም
ከክልሉ መንግስት ጋር በመቀናጀት ታፍነው የተወሰዱ ህፃናትን ለማስመለስ ከዲፕሎማሲያዊ ስራዎች ባለፈ ለጀግናው
የመከላከያ ሠራዊታችን ታላቅ ተልዕኮ በመስጠት ውጤታማ ግዳጅ እንዲፈፀም ማስቻሉን ተናግረዋል፡፡
No comments:
Post a Comment